6730 Rainier Ave S Amharic

ጀቦዳ ፕሮፐርቲስ እና ጄደብልዩ አርክቴክቶች የ6730 እና 6724 ሬይነር አቬኒዩ ሳዉዝ ልማት ለመንደፍ እየተባበሩ ነዉ። ሲጠናቀቅ በጠቅላላ 26 አዲስ ቤቶች ይኖራሉ። ፕሮጄክቱ 25 የመኪና ማቆሚያዎች ጋር 3 ፎቆች ከፍታ ያለዉ ይሆናል። አሁን ገና ማቀድ መጀመራችን ነዉ – ግንባታ በበልግ ወቅት 2022 ሊጀምር የሚችል እና ህንጻዉ በ2023 በጋ ወቅት ፈጥኖ ክፍት ሊሆን ይችላል።

ይህ ጥናት ከዚህ (09-09-2021) ጀምሮ እስከ (09-30-2021) ድረስ ክፍት ይሆናል። ጥናቱ ሲጠናቀቅ ለከተማው ዲዛይን ግምገማ  እና  ሌሎች ፍቃድ ለማግኘት የሚደረጉ ጥረቶች ዝግጅት ማድረግ እንጀምራለን።

ስለዚህ ፕሮጀክት ተጨማሪ መረጃ ለማግኘትም ሆነ ለዲዛይን ግምገማና ፍቃድ ለማግኘት የሚደረገውን ሂደት ለመከታተል ከፈለጉ የፕሮጀክቱን አድራሻ (6730 & 6724 Rainier Ave S) ወይንም Design Review Calendar የ ፕሮጀክት ቁጥር (3038313-EG) እና Seattle Services Portal. ይመልከቱ። ለ ዲዛይን ግምገማ ስለሚደረገው የቅድሚያ ተደራሽነት ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ድህረ ገጻችንን Department of Neighborhood’s webpage ይጎብኙ።

ለመጠይቁ የሚሰጡት መልስ በሚስጥር ላይያዝ ስለሚችል እባክዎን በዚህ መጠይቅ ውስጥ የግል መረጃዎን፣ ስምዎን ወይንም ማናቸውም አይነት ማንነትን የሚገልጹ መረጃዎችን አያካትቱ።

Take Survey

Download Flyer